
የተባበሩት መንግሥታት በሰሜን ጎንደር የተፈጸመውን የቀይ መስቀል ባልደረባ "አሰቃቂ ግድያ" አወገዘ
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ባልታወቁ ሰዎች ታግቶ በተፈጸመበት ድብደባ ሕይወቱ ያለፈውን የቀይ መስቀል ባልደረባ ሆነልኝ ፋንታሁንን "አሰቃቂ ህልፈት" አወገዘ። "የረድዔት ሠራተኞች የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ አይገባም" ሲሉ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ (ኦቻ) ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ዶክተር አቡባካር ካምፖ መናገራቸውን ቢሮው ገልጿል።
Read the full story