
ግብፅ በናይል ተፋሰስ ላይ "ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ የተናጠል እርምጃን" እንደማትቀበል ለበርካታ የአፍሪካ አገራት አስታወቀች
የሕዳሴ ግድብ በመጪው መስከረም ይመረቃል መባሉን ተከትሎ ግብፅ "የዓለም አቀፍ ሕግን በጣሰ መልኩ በምሥራቃዊ ናይል ተፋሰስ የሚደረግ የተናጠል እርምጃን" እንደማትቀበል ለበርካታ አፍሪካ አገራት አሳወቀች። የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ የናይል ተፋሰስ አገራት ከሆኑት ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከኡጋንዳ፣ ከኬንያ እንዲሁም ከተፋሰሱ ውጭ ካሉት ከጂቡቲ እና ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በተናጠል ባደረጉት የስልክ ውይይት ነው ይህንን ያስታወቁት።
Read the full story