የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው የፋይናንስ ፍላጎት ከባንኮች አቅርቦት በላይ እንደሆነ ተገለጸ
ችግሩ ከውጭ በሚገቡ ባንኮች በዘላቂነት ይፈታል ተብሏል በኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው የፋይናንስ ፍላጎት ከባንኮች አቅርቦት በላይ መሆኑን፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ይህንን ያስታወቀው የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በተዘጋጀው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር...