በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ያለውን የመድኃኒት ዋጋ ለማረጋጋት መንግሥት እያቀረበ መሆኑ ተገለጸ
የብር የመግዛት አቅም በመዳከሙ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኘውን የመድኃኒት አቅርቦት ዋጋ ለማረጋጋትና ተመጣጣኝ ለማድረግ፣ መንግሥት አስፈላጊና ውድ የሚባሉትን ጨምሮ መድኃኒቶችን በበቂ ሁኔታ እያስገባሁ ነው አለ፡፡ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አብዱልቃድር ገልገሎ (ዶ/ር)፣...