
በኖርዌይ ኢትዮጵያዊቷን 'በዘረኝነት ተነሳስቶ' በስለት የገደላት ግለሰብ በሽብር እንደሚጠየቅ ተዘገበ
በኖርዌይ የ34 ዓመቷን ኢትዮጵያዊ የማኅበራዊ ሠራተኛ (ሶሻል ወርከር) 'በዘረኝነት ተነሳስቶ' በተደጋጋሚ በስለት ወግቶ የገደላት የ18 ዓመት ግለሰብ ከግድያ በተጨማሪ በሽብርተኝነት ሊከሰስ ነው። ታሚማ ኒብራስ ጁሃር የተባለችው ይህች ኢትዮጵያዊት ትሠራበት በነበረው የታዳጊዎች ማዕከል ውስጥ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በተደጋጋሚ በስለት ተወግታ መገደሏን ባለሥልጣናት ሰኞ ዕለት ማስታወቃቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
Read the full story