በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያንን እንቅስቃሴ የገታው ውሳኔ እና የመንግሥት ምላሽ
ኬንያ በአነስተኛ የንግድ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የውጭ ዜጎችን ሥራ የምታስቆምበት ቀን ሰኞ ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም. መጀመሩን ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የንግድ ቤቶቻቸውን ዘግተው ውለዋል። ወደ አገራቸው ለመመለስ በመጣደፍ ላይ ያሉ የሌሎች አገራት ዜጎችም በርካታ ናቸው። የኬንያ መንግሥት በበኩሉ፣ የፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶን መመሪያ ተከትሎ የተፈጠረውን ጭንቀት አላስፈላጊ እና ማንንም የሚያሰጋ እንዳልሆነ ለቢበሲ ገልጿል።









