ግመሎችን እና ወርቅ በመሸጥ ሃብት ያካበቱት፣ አሁን ደግሞ ከፊል ሱዳንን የሚቆጣጠሩት ሐምዳን ዳጎሎ
ሞሐመድ ሐምዳን ዳጎሎ ወይም "ሄሜቲ" ከሚመሩት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጋር በመሆን በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኑ እና አሁን የአገሪቱን ግማሽ የሚቆጣጠሩ ግለሰብ ናቸው። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የአገሪቱ ጦር እና አጋሮቹ በምዕራብ ዳርፉር የምትገኘውን የጦሩ መቀመጫ የኤል ፋሸር ከተማን በእጁ ሲያስገባ አስደናቂ ድል አግኝቷል።
