በአርሲው ጥቃት እናት እና ሦስት ልጆችን ጨምሮ ስምንት ሰዎች የተገደሉበት ቤተሰብ
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ውስጥ በአንድ ሳምንት ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች ሕጻናትን ጨምሮ "25 ሰዎች" መገደላቸውን የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና በአካባቢው የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች ተናገሩ። ባለፈው ሳምንት ረዕቡ እና ሐሙስ ዕለት በተፈጸመው የመጀመሪያው ጥቃት ከተገደሉ ሰዎች ውስጥ "ስምንቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት" እንደሆኑ ሦስት ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል።

