የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት በምስል

The latest stories from Ethiopia's trusted newsrooms, gathered in one place.
Updated throughout the day



ግንባታው 14 ዓመታትን የፈጀው እንዲሁም አምስት ቢሊዮን ዶላር ገደማ የተበጀተለት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ማክሰኞ፣ ጳጉሜ 4/ 2017 ዓ.ም ተመርቋል። የናይልን 55.ሚሊዮን ኪዩቢክ ውሃን የምትጠቀመውና ለዓመታት ኢትዮጵዮያ ግድብ እንዳትገነባ ስትከላከል የነበረችው ግብፅ የግድቡን ግንባታ ከጅምሩ ተቃውማዋለች። በሕዳሴ ግድብ የተካሄዱ አምስት የውሃ ሙሌቶችም ከግብፅ በኩል ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎችን ያስከተሉ ናቸው።




ኢትዮጵያ ባለፉት 14 ዓመታት ስትገነባው የነበረውን ግድብ ባስመረቀችበት ዕለት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያን የተናጠል እርምጃን በመቃወም ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት የአቤቱታ ደብዳቤ አስገቡ። ባለፉት ዓመታት የግድቡን ውሃ አሞላል እና ቀጣይ ሥራን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ በግብፅ እና በሱዳን መካከል ተደጋጋሚ ንግግሮች ቢካሄዱም ከሚያስማማ ነጥብ ላይ ሳይደረስ የግድቡ ግንባታ ተጠናቅቆ በይፋ ተመርቋል።
