የየመን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከፍተኛ ባለሥልጣናት በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ
በየመን በሁቲ የሚመራው መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ራሃዊ እና ሌሎች በርካታ ሚኒስትሮች እስራኤል በዋና ከተማይቱ ሰነዓ ላይ በፈጸመችው ጥቃት መገደላቸውን የሁቲ ከፍተኛ ኃላፊ አስታወቁ። እስራኤል ሐሙስ ዕለት በሰነዓ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ሌሎች በርካቶች መቁሰላቸውን ባለሥልጣኑ ጨምረው ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት ሁቲዎች ወደ እስራኤል ክላስተር ቦምብ የያዘ ሚሳዔል ማስወንጨፋቸውን ተከትሎ የእስራኤል ጦር ሰነዓ ውስጥ የሁቲ ዒላማዎችን መምታቱን አስታውቋል።

