አቶ ታዬ ደንደአ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው መወሰዳቸውን ባለቤታቸው ተናገሩ
የቀድሞው የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ በዛሬው ዕለት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለቤታቸው ተናገሩ። ከሥልጣናቸው ተነስተው ለረጅም ጊዜ በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ በዋስትና ተለቀው ጉዳያቸውን ከውጪ ሲከታተሉ የነበሩት አቶ ታዬ ዛሬ በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት በቀጠሯቸው መሠረት ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።
