የጄኔራል አል ቡርሐን መቀመጫ በሆነችው ፖርት ሱዳን ለሦስት ተከታታይ ቀናት የድሮን ጥቃት ተፈጸመ
በሱዳን ወታደራዊ ኃይል የሚመራው መንግሥት መቀመጫ በሆነችው የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ለሦስተኛ ተከታታይ ቀን የድሮን ጥቃት ተፈጸመባት። በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አይሎ አብዛኛውን ካርቱም ሲቆጣጠር በጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው የአገሪቱ ጦር ኃይል መቀመጫውን ወደ ፖርት ሱዳን አዙሮ ቆይቷል።
