BBC Amharic·
አምስት ጊዜ ለኬንያ ፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው ያልተሳካላቸው ራይላ ኦዲንጋ አረፉ
ዝነኛው ኬንያዊ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ በ80 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ኦዲንጋ በሕንድ ሕክምና እየተከታተሉ እንደነበር ተገልጿል። ለአሥርታት የዘለቀው የፖለቲካ ሕይወታቸው ቤተ መንግሥት አላደረሳቸውም። ኬንያ ከእንግሊዝ ነፃ ስትወጣ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ያገለገሉት አባታቸውም ዋናውን መንበር ማግኘት አልቻሉም። ኦዲንጋ አምስት ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድረዋል። መራጮች ግን ፊታቸውን እንዳዞሩባቸው ቆይተዋል።