በትግራይ የሚካሄደው የግዳጅ ምልመላ፡ ከክልሉ የሚሸሹ እና ለመደበቅ የተገደዱ ወጣቶች
በትግራይ እየተካሄደ ያለው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በፈጠረው ስጋት ምክንያት በርካታ ወጣቶች ከክልሉ እየወጡ ወደ ቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል እየሸሹ ሲሆን ሌሎች ደግሞ እዚያው ተደብቀው እንደሚገኙ ተናገሩ። አፈሳው ከነዋሪዎች እና ከመብት ድርጅት ውግዘት እየገጠመው ቢሆንም በፈቃደኝነት የሚካሄድ ነው በማለት ህወሓት አስተባብሏል።









