የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የተካሄደው መቶ በመቶ በኢትዮጵያውያን ገንዘብ ነው - ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ግዙፉ የሕዳሴ ግድብ መቶ በመቶ የተገነባው "ያለምንም የውጭ እርዳታም ሆነ ብድር በራስ አቅም"፣ መሆኑን አስታወቀ። ጽህፈት ቤቱ ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች ባሠራጨው መግለጫ ላይ መላው ኢትዮጵያውያን ግድቡ ግንባታ ሂደት ውስጥ "በሞራል፣ በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በዕውቀት" መሳተፈቸውን ጠቅሷል።
