"የ2010ሩ ተስፋ፣ አምባገነናዊ መንግስት ለመገንባት በታቀደ ፕሮጀክት ተከድቷል" - ኦፌኮ
ተቃዋሚው የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከሰባት ዓመታት በፊት "በታሪካዊ ዴሞክራሲያዊ መደላድል ተስፋ" የተጀመረው "ለውጥ" " 'የባከነ ተስፋ' ዜና መዋዕል ሆነው ተጠናቋል" አለ። ፓርቲው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን መምጣት የተጀመረው "ተስፋ"፤ "አምባገነናዊ መንግስት ለመገንባት በታቀደ ፕሮጀክት ተከድቷል" ሲል ተችቷል።



