The latest stories from Ethiopia's trusted newsrooms, gathered in one place.
Updated throughout the day



ሰዎች ለተለያዩ ምግቦች አለርጂ መሆናቸውን በስፋት ሲናገሩ ይሰማል። እነዚህ ሰዎች የማይስማማቸውን ምግብ ከተመገቡ የሰውነት መቆጣትን ጨምሮ መታመም ይገጥማቸዋል። ከዚህ ባሻገር አንዳንድ ሰዎች ከሰዎች ጋር በሚኖራቸው ንክኪ ምክንያት የሚቀሰቀስ አልርጂ እንዳለባቸው ያውቃሉ?


የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የስር ፍርድ ቤቶች ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዛትን ለማገድ የሚያስችላቸው ሥልጣን ውስን እንዲሆን በየነ።

ኢራን ለ12 ቀናት በዘለቀው የእስራኤል ግጭት የተገደሉ ወታደራዊ አዛዦች እና የኒውክሌር ሳይንቲስቶችን ጨምሮ 60 ለሚሆኑ ዜጎቿ ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት እያካሄደች ነው።የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው እየተፈጸሙ ካሉ መካከል የኢራን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የሆኑት መሐመድ ባግሔሪ አንዱ ናቸው።

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ልጆቻቸው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ይዘት ያላቸው መጻህፍትን እንዲያነቡ አንፈልግም ላሉ ወላጆች፤ ይህንን የሚያስችል ውሳኔ አሳለፈ።

በአሜሪካ እና በእስራኤል የሚደገፈው አወዛጋቢው የእርዳታ ድርጅት ኃላፊ በተደጋጋሚ እርዳታ በመጠባበቅ ላይ በሚገኙ ፍልስጤማውያን ላይ በእስራኤል ጥቃት ግድያ እና ጉዳት ከተፈፀመ በኋላ "ሥራቸውን በአግባቡ እየሰሩ" እንደሆነ ተናገሩ።
