የኢትዮጵያ ባለስልጣናት "የጤና ባለሙያዎችን በማዋከብ የአገሪቱን የጤና ችግር መፍታት አይችሉም"- ሂውማን ራይትስ ዋች
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት "የጤና ባለሙያዎች ማህበርን በማገድ፣ ባለሙያዎችን በማሰር እና በማዋከብ አሳሳቢ የሆነውን የአገሪቱን የጤና ችግር መፍታት እንደማይችሉ" የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪው ሂውማን ራይትስ ዋች ገለጸ።

The latest stories from Ethiopia's trusted newsrooms, gathered in one place.
Updated throughout the day
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት "የጤና ባለሙያዎች ማህበርን በማገድ፣ ባለሙያዎችን በማሰር እና በማዋከብ አሳሳቢ የሆነውን የአገሪቱን የጤና ችግር መፍታት እንደማይችሉ" የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪው ሂውማን ራይትስ ዋች ገለጸ።

ኤርትራ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት "ለጦርነት አጀንዳው ድጋፍ ለማሰባሰብ"፤ የከፈተውን "ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ አጠናክሮብኛል" ስትል ከሰሰች። የኢትዮጵያ መንግሥት "ባለፉት ቀናት" ኤርትራን የሚከስሱ ደብዳቤዎችን ወደ "የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ" እና "የሀገራት መሪዎች ልኳል" በማለትም ወቅሷል።


የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሙስና የተከሰሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ክሳቸው ውድቅ ተደርጎ "ምህረት" እንዲደረግላቸው እስራኤልን ጠየቁ።

የኬንያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ረቡዕ ፣ሰኔ 18/ 2017 ዓ.ም በመላ አገሪቱ የተካሄደውን ተቃውሞ "ሰላማዊ መስሎ የታየ የሽብር ተግባር" እና "የመንግሥት ለውጥ ለማድረግ የተደረገ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ሙከራ" ነው አሉ።

የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ይዞታዎች ላይ በፈጸመችው ጥቃት "ምንም አላተረፈችም" ሲሉ ተናገሩ። ኻሜኒ ከእስራኤል ጋር ግጭት ከቆመ በኋላ በሰጡት የመጀመሪያ መግለጫቸው "የአሜሪካ ጥቃት የኢራንን የኒውክሌር መርሃግብር ለማደናቀፍ ያቀደውን ስኬት አላገኘም" በማለት ገልጸዋል።


