የውጭ ሀገር ተጓዦች ማግኘት የሚችሉት የውጭ ምንዛሪ መጠን በእጥፍ አደገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ የግል ተጓዞች እንዲያገኙ የሚፈቀድላቸውን የውጭ ምንዛሪ መጠን ከአምስት ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወደ 10 ሺህ ዶላር አሳደገ። ባንኮች ለሚሰጧቸው የውጭ ምንዛሪ አገልግሎቶች የሚያስከፍሉት የገንዘብ መጠንም "ከአራት በመቶ እንዳይበልጥ" እንዲሁም "ጥቃቅን የአገልግሎት ወጪዎችን እንዲያስቀሩ" መወሰኑንም አስታውቋል።

