ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከተስማሙ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞቃዲሾን ሊጎበኙ ነው
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለአንድ ዓመት የቆየውን ውዝግባቸውን በድርድር ከፈቱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሞቃዲሾ በማምራት ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ተነገረ። የሁለቱ አገራት መሪዎች በቱርክ ፕሬዝዳንት አቀራራቢነት አንካራ ላይ ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሚያደርጉት ጉብኝት የአገራቱን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።




