በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል "ዘላቂ የሰላም ስምምነት" ተፈረመ
በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂ የፋኖ ቡድኖች አንዱ የሆነው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ከክልሉ መንግሥት ጋር የዘላቂ ሰላም ስምምነት መፈራረሙ ተገለጸ። የሰላም ስምምነቱ እንዲፈረም በማደራደር የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) መሳተፋቸውም ተነግሯል።
