ቲክቶክ ገዢ ካላገኘ ወይም ስምምነት ላይ ካልተደረሰ በአሜሪካ ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ ይዘጋል

The latest stories from Ethiopia's trusted newsrooms, gathered in one place.
Updated throughout the day




የአማራ ክልል ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ ተማሪዎች የግእዝ ቋንቋን ማስተማር እንደሚጀምር አስታውቋል። ይህ ውሳኔ ከተለያዩ አቅጣቻዎች የድጋፍ እና የተቃውሞ ሃሳብ እየተሰነዘረበት ነው። ቢቢሲ ወላጆች እንዲሁም የቋንቋ እና የትምህርት ምሁራን የግእዝ ቋንቋን እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት በመስጠት ዙሪያ ያላቸውን አስተያየት እና ሃሳብ ጠይቋል። ይህንን ቀደምት ቋንቋ ማስተማርን እንዴት ይመለከቱታል?

በአዲስ አበባ ዛሬ እሁድ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በማስመልከት ለተዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ትርዒት ለማቅረብ ቅዳሜ ምሽት ልምምድ ላይ የነበሩ ልጆች ላይ መድረክ ተደርምሶ ጉዳት ደረሰባቸው። ታዳጊዎቹ የሕዳሴውን ግደብ መጠናቀቅ ተከትሎ ለከተማዋ ነዋሪዎች እና ለተጋባዥ እንግዶች ትርዒት ለማቅረብ እየተዘጋጁ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

በጃፓን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በማራቶን የብር ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነችው አትሌት ትዕግሥት አሰፋ ወርቅ አጣሁ ብዬ ማሰብ አልፈልግም አለች። በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት ትዕግሥት አሰፋ 2ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን ተከትሎ ነው ይህንን የተናገረችው። አትሌት ትዕግስት ከኬንያዊቷ አትሌት ፔሬስ ጂፕችርችር ጋር ብርቱ ፉክክር አድርጋ ነው የብር ሜዳሊያ ለአገሯ ያስገኘችው።



