በኬንያ ትናንት በነበረ ተቃውሞ በትንሹ 11 ሰዎች ተገደሉ

The latest stories from Ethiopia's trusted newsrooms, gathered in one place.
Updated throughout the day


ባለፈው ዓመት በሳዑዲ አረቢያ ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በውጪ ዜጎች ላይ የሚፈጸም የሞት ቅጣት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አምነስቲ ገለፀ። ሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ዓመት 345 ሰዎችን በሞት የቀጣች ሲሆን ይህም አምነስቲ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ከመዘገበው ከፍተኛው ቁጥር ነው ብሏል። ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ 180 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል ያለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኑ፣ ይህም ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመልክቷል።




ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ የሚሰበሰበው ከፍተኛው 35 በመቶ ታክስ፤ መቆረጥ የሚጀምርበት የደመወዝ እርከን ከ10,900 ብር ወደ 14 ሺህ ብር ከፍ እንዲል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። ይህ ከፍተኛ ግብር መቆረጥ የሚጀምርበት የደመወዝ እርከን ከዚህ በላይ ከፍ ያልተደረገው "በተለይ በክልል መንግሥታት ገቢ ላይ ከፍተኛ ጫናን ስለሚሳያድር" እንደሆነ ተገልጿል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያን ጨምሮ 11 አባላትን ካቀፈው የብሪክስ ጥምረት ፖሊሲዎች ወግነው ከአሜሪካ ጥቅም የሚጻረሩ አገራት ተጨማሪ 10 በመቶ ታሪፍ እንደሚጣልባቸው አስጠነቀቁ።

በኬንያ ዛሬ ሰኞ፣ ሰኔ 30/ 2017 ዓ.ም ከታቀደው ተቃውሞ በፊት የአገሪቱ ጸጥታ ኃይሎች የማዕከላዊ ናይሮቢ መግቢያ እና መውጫ ሁሉንም ዋና መንገዶችን ዘጉ።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ የቅርብ አጋራቸው ቱጃሩ ኤለን መስክ አዲስ የፖለቲካ ለመመስረት ማቀዱን፤ በአሜሪካ ያለው የሁለት ፓርቲ ስርዓት ነው በማለት "አስቂኝ" ሲሉ አጣጣሉ።
