በኢትዮጵያ "ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለረሃብ" መጋለጣቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ
በኢትዮጵያ "ከአስር ሚሊዮን በላይ" ሰዎች በሀገሪቱ "እየጨመረ ላለው ረሃብ እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት" መጋለጣቸውን የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ። ፕሮግራሙ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚያከናውነው ሥራ የሚውል ተጨማሪ ገንዘብ በአስቸኳይ የማያገኝ ከሆነ "ለ3.6 ሚሊዮን" ሰዎች የሚያቀርበውን "የነፍስ አድን ምግብ" ድጋፍ "በመጪዎቹ ሳምንታት" እንደሚያቋረጥ አስጠንቅቋል።

