አስር ሴቶች፣ አንድ ወንድ፡ በኢትዮጵያ አነጋጋሪ የሆነው የመተጫጨት የቴሌቪዥን ሾው 'ላጤ'
አንድ ወንድ እና ሴት ይገናኛሉ። ሴቲቱ በወንዱ ፍቅር ትወድቃለች። በወንዱ ዙሪያ የሚያንዣብቡ እና በፍቅር ለመማረክ የሚሞክሩ ተቀናቃኞችን ትከላከላለች። በስተመጨረሻም ወንዱ ለፍቅሯ እጁን ይሰጣል። ይህ በዩቲዩብ ሲቀርብ የነበረው ትርዒት ባለፉት ወራት በኢትዮጵያውያን ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። በርካቶች ከባህል ተቃራኒ ነው ብለው ሲተቹ፣ ሌሎች ደግሞ በአውንታዊ መልኩ ድጋፋቸውን ሲገልጹ ነበር።


