ለ43 ዓመታት አድማጮቹን ያገለገለው እና በድንገት በትራምፕ ውሳኔ የተዘጋው ቪኦኤ አማርኛ
ቪኦኤ አማርኛ ለ43 ዓመታት ለኢትዮጵያውያን አድማጮቹ የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያቀርብ ከቆየ በኋላ ከመጋቢት 7/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ስርጭቱን ሙሉ በሙሉ አቋርጧል። በዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ስርጭቱን ያቋረጠው ቪኦኤ በመላው ዓለም 400 ሚሊዮን አድማጮች ነበሩት። ለመሆኑ የኢትዮጵያ አድማጮቹን በአማርኛ፣ ኦሮምኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎች እያገለገለ የነበረው ቪኦኤ ከምስረታው እስከ አሁን ድረስ ያለፈበት ሁኔታ ምን ይመስላል? የቪኦኤ መቋረጥ የኢትዮጵያ አድማጮችን ምን ያሳጣል?
