ለጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ተሰጥቶ የነበረው ቦታ ለኦሮሚያ ባህል ማዕከል ተላለፈ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውሳኔው የከተማ አስተዳደሩ ነው ብሏል በአዲስ አበባ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ከአንድ ዓመት በፊት ተሰጥቶ የነበረው 12 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ፣ ለኦሮሚያ ባህል ማዕከል ማስፋፊያ ፕሮጀክት...

The latest stories from Ethiopia's trusted newsrooms, gathered in one place.
Updated throughout the day
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውሳኔው የከተማ አስተዳደሩ ነው ብሏል በአዲስ አበባ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ከአንድ ዓመት በፊት ተሰጥቶ የነበረው 12 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ፣ ለኦሮሚያ ባህል ማዕከል ማስፋፊያ ፕሮጀክት...

በስኮትላንድ ግላስጎው አሜን ተክላይ በተባለ ታዳጊ ግድያ ጋር በተያያዘ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የ14 እና የ15 ዓመት እድሜ ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

አሠራሩ የአርሶ አደሮችን ዓመታዊ ገቢ ከፍ ያደርጋል ተብሏል በሃይማኖት ደስታ ለአርሶ አደሮች 129 በመቶ የገቢ ዕድገት ያስገኘላቸው ዘመናዊ የግብርና አሠራር በታሰበው ልክ እንዳይተገበር፣ ከላይ እስከ ታች ያለው የመንግሥት መዋቅር ክፍተት መፍጠሩ ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የግብርና ሚኒስቴር ከጃፓን...

የሶሪያ የጸጥታ ኃይሎች በአገሪቱ የባሕር ዳርቻ አካባቢው በቀጠለው አለመረጋጋት በመቶዎች የሚቆጠሩ የአላዋይት ማኅበረሰብ አባላትን ገድለዋል የሚል ውንጀላ ቀረበባቸው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ የፍጆታ የአገልግሎት ታሪፍ ተመን ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑ ታወቀ፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ በመኖሪያ ቤት ታሪፍ ላይ 0.50 ኪሎ ዋት ሰዓት የሚጠቀሙ...
ሩስያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት ቢያንስ 25 ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ ባለስልጣናት ተናገሩ። በዶኔትስክ ግዛት በተፈፀመ አንድ ጥቃት በትንሹ 11 ሰዎች ሲገደሉ፣ የስድስት ዓመት ሕጻንን ጨምሮ 40 ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ቅዳሜ ዕለት ተናግረዋል።

በአሜሪካ ከአስራ አምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ አንድ ሞት የተፈረደበት እስረኛ በአልሞ ተኳሾች በጥይት አርብ ዕለት ተገድሏል። የደቡብ ካሮላይና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ብራድ ሲግሞን የተሰኘው ፍርደኛ የሞት ቅጣቱ በጥይት ተፈጻሚ እንዲሆንበት ብይኑን ረቡዕ ዕለት ነበር ያስተላለፈው።

ታዋቂዋ ደራሲ ቺማማንዳ ንጎዚ አዲቼ የመጀመሪያ ልጇን አርግዛ በነበረበት ወቅት "አስደንጋጭ በሆነ መልኩ መጻፍ አልቻልኩም ነበር" ትላለች። "በዚህ ሁኔታ ላይ መገኘት በጣም አስፈሪ ነው። ምክንያቱም ለሕይወቴ ትርጉም የሚሰጠኝ መጻፍ ብቻ ነው" ስትል የ47 ዓመቷ ተወዳጇ ናይጄሪያዊት ደራሲ ለቢቢሲ ተናግራለች።

በመላው ዓለም ቁልፍ በሚባሉ የሙያ መስኮች ላይ ሴቶች ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ ነው። በተለይ ደግሞ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢንጅነሪንግ እና በሒሳም የትምህርት መስኮች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሴቶች ቁጥር በጣም አናሳ ነው። ይህ ሴቶች ተፈላጊ በሆኑት በእነዚህ መስኮች ላይ ያላቸው ሚና በአፍሪካ ውስጥም ተመሳሳይ ገጽታ ነው ያለው። በኢትዮጵያ እና በሌሎች የአፍሪካ አገራት ሴቶች በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መስኮች ያላቸው ተሳትፎ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳሰዋል።
