በኢትዮጵያ እና በሌሎች አገራት የተቋረጠውን የአሜሪካ እርዳታን ቻይና ትሸፍን ይሆን?
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ሥልጣን በመጡ ማግስት ከወሰዷቸው እርምጃዎች መካከል አሜሪካ በተለያዩ ዘርፎች በመላው ዓለም የምታቀርበው እርዳታ እንዲቆም ማድረግ አንዱ ነው። ይህ ውሳኔ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ አገራት ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ጉልህ ከፍተትን ፈጥሯል። የአሜሪካ ዋነኛዋ ተፎካካሪ አገር የሆነችው ቻይና ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የተጽእኖ ክልሏን ልታሰፋ የምትችልበት ዕድል እንደሚፈጥርላት እየተነገረ ነው።



