በካናዳ አየር ማረፊያ አውሮፕላን ተገልብጦ ሶስት ሰዎች ቢጎዱም የሞት አደጋ እንዳልተከሰተ ተዘገበ

The latest stories from Ethiopia's trusted newsrooms, gathered in one place.
Updated throughout the day

ስማርት ስልኮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተራቀቁ ቢመጡም፣ አነስተኛ ጥቅም የሚሰጡ ቀደምት ስልኮችን የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። የስማርት ስልኮችን ገጽታ የለወጠው አይፎን ገበያ ላይ ከዋለ 17 ዓመት ይዟል። ያሁኑ ትውልድ ያለ ስማርት ስልክ ሕይወት ምን ሊመስል እንደሚችል አያውቅም። ነገር ግን ለመደወል እና የጽሁፍ መልዕክት ለመለዋወጥ ብቻ የሚያገለግሉ ስልኮች ተፈላጊነት እየጨመረ ነው።


በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ካለፈው ሳምንት ሐሙስ ጀምሮ በተፈፀመ ጥቃት ሰዎች ሲገደሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ደግሞ መፈናቀላቸው ነዋሪዎች ተናገሩ። በዞኑ ጌራ ወረዳ ዋላ በተባለ ቀበሌ የካቲት 6/2017 ዓ.ም. አቶ ዛኪር አባ ኦሊ የተባሉ ባለሀብት መገደላቸውን ተከትሎ "ወጣቶች" የነዋሪዎችን ማንነት እየለዩ ቤቶችን እና ንብረቶችን ማቃጠላቸውን የዓይን እማኞች እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

An ambitious startup is working on tokenization of coffee in Ethiopia powered by Ethereum's blockchain. Waga looks to leverage smart contracts and IoT's in the endeavor. By Etenat AwolRefraining from disclosing exact expenditure, the CEO revealed that nearly 235 million dollars in investments had been mobilized and deployed by mid-year. By Team Shega


በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ውስጥ በሚገኙ አራት ወረዳዎች ውስጥ በተከሰተ "የአጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት" በሽታ ምክንያት በአንድ ሳምንት ውስጥ ህጻናትን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔ ምክንያት "አገር አልባ ለመሆን ተቃርቤያለሁ" ሲሉ ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ተናገሩ። ባለፈው ሳምንት ሰኞ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ወደ አገር ቤት እንዳይገቡ የተከለከሉት አቶ ልደቱ "ይህ እገዳ ከበኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጨማሪ ኢትዮጵያ በሚበሩ ሌሎች አየር መንገዶች ላይም ጭምር መሆኑን ደርሼበታለሁ" ብለዋል።

የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም አሜሪካ እና ሩሲያ በሚያደርጉት የሰላም ንግግር አገራቸው አለመጋበዟን የዩክሬን መንግሥት ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑ አንድ ምንጭ ለቢቢሲ ተናገሩ።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፍልስጤማውያንን ከመሬታቸው ጋዛ አፈናቅሎ ወደ ሌሎች አገራት ለማስፈር የያዙት እቅድ "እውን ለማድረግ" እየሰሩ መሆኑን ተናገሩ።
