የሱዳን ጦር ካርቱምን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ገለፀ
የሱዳን ጦር ኃይሎች አዛዥ፣ አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጦራቸው በካርቱም የሚገኘውን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ካስለቀቀ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ "ካርቱም ነጻ ናት" ሲሉ አወጁ። ጀኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ጦሩ በካርቱም የሚገኘውን የአገሪቱን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከተቆጣጠረ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በስፍራው የደረሱ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥትንም ጎብኝተዋል።



