አሜሪካ ዋጋ ለማቃለል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንቁላሎችን ከቱርክ እና ደቡብ ኮሪያ ልታስገባ ነው
የትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ በከፍተኛ ሁኔታ የናረውን የእንቁላልን ዋጋ ለማቃለል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንቁላሎችን ከቱርክ እና ደቡብ ኮሪያ ሊያስገባ ነው።

The latest stories from Ethiopia's trusted newsrooms, gathered in one place.
Updated throughout the day
የትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ በከፍተኛ ሁኔታ የናረውን የእንቁላልን ዋጋ ለማቃለል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንቁላሎችን ከቱርክ እና ደቡብ ኮሪያ ሊያስገባ ነው።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪው ኡበር በዩናይትድ ኪንግደም የሴት አሽከርካሪዎቹን ቁጥር ለመጨመር በየሳምንቱ 20 ሰዓታት ነጻ የልጅ እንክብካቤ እንዳዘጋጀ አስታወቀ።

የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር ሃማስ የተቀሩትን ታጋቾች በሙሉ እስካልለቀቀ ድረስ ወታደሩ "በጋዛ ተጨማሪ ቦታዎችን እንዲወር" እንዲሁም የተወሰኑ ክፍሎችን በቋሚነት እንደሚይዝ ዛቱ።

በዩናይትድ ኪንግደም ግዙፉ የሆነው ሂትሮው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በረራ መጀመሩን እና ቅዳሜ ዕለት ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ገለፀ። አየር ማረፊያው አቅራቢያ የሚገኝ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የተቀሰቀሰን እሳት ተከትሎ በተከሰተው መብራት መቋረጥ አርብ ዕለት ሙሉ ቀን ተዘግቶ ውሏል።

የሱዳን ጦር ወታደሮች የፕሬዝዳንቱን ቤተ መንግሥት መቆጣጣራቸውን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ካርቱም የሚያሳዩት ፈንጠዝያ እንዲሁም በቅርብ ወራት ውስጥ የተለያዩ ግዛቶችን መቆጣጠራቸው ወሳኝ የማጥቃት እርምጃ ላይ መሆናቸውን ያሳያል። የሱዳን ጦር ኃይሎች በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ ዋና ከተማይቱን መቆጣጠር ተስኗቸው ከፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF) እጅ ፈልቅቆ ለማውጣት ለሁለት ዓመታት ሲዋጉ ቆይተዋል።

ፊንላንድ ለስምንት ተከታታይ ዓመት በዓለም ደስተኛ ሀገር ሆና ተመርጣለች። የተፈጥሮ መዳረሻ ከመሆን እና ጠንካራ የማሕህበራዊ ዋስትና ስርዓትን መዘርጋቷ ደስተኛ አገር ሆና ለመመረጧ ምክንያት እንደሆነ ባለሙያዎች ተናግረዋል።


በሱዳን ኢትዮጵያዊያን፣ በተለይም በትግራይ ጦርነት የተፈናቀሉ በሚኖሩበት መጠለያ ጣቢያ በተከሰተ የእሳት አደጋ ምክንያት ሁለት ሕፃናት ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል። ቃጠሎው የተከሰተው ከመጠለያ ጣቢያዎች መካከል አንዱ በሆነው ኡምራ ኩባ እንደሆነ የሱዳን ነዋሪ የሆነው ጋዜጠኛ መድኃኔ ግደይ ለቢቢሲ ተናግሯል

በኤሎን መስክ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኩባንያ የሚመረተው ቴስላ መኪናን ላይ ያነጣጠረ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ሶስት ተከሳሾች እስከ 20 ዓመት እስር እንደሚጠብቃቸው የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጄነራል ፓም ቦንዲ ተናገሩ።

The initiative is supported by the Gates Foundation and aligns with the Ethiopian government's Digital Agriculture Roadmap. By Team ShegaEthiopia has been pursuing debt restructuring under the G-20 Common Framework (CF) since February 2021 with a creditor committee comprising 12 countries. By Etenat Awol
