ኢንሱሊን መላመድ ምንድን ነው? በፆም ወቅትስ እክል ይፈጥራል?
በጡንቻ፣ በስብ እና በጉበት ውስጥ ያሉ ሕዋሳት ለኢንሱሊን መስጠት ያለባቸውን ምላሽ ሲያስተጓጉሉ ኢንሱሊን መላመድ ተፈጥሯል ማለት ነው። ከደም ውስጥ ጉሉኮስ ወስዶ ማከማቸት እንዲሳናቸው ያደርጋል።

The latest stories from Ethiopia's trusted newsrooms, gathered in one place.
Updated throughout the day
ከእጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ጋር በተያያዘ ከሁለት ቀናት በፊት በቁጥጥር ስር የዋለው ሙዚቀኛው አንዱዓለም ጎሳ ፍርድ ቤት ቀረበ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት በዛሬው እለት በአዲስ አበባ እየሰጡ ባሉት መግለጫ፣ አዲስ አበባ የመጡት በክልሉ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ከፌደራሉ መንግስት ጋር ለመወያየት እንጅ ጣልቃ እንዲገባ ለመጠየቅ አለመሆኑን ተናገሩ። በመግለጫቸውም የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ የቀረበ...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ "ለራሱ የግል እና የቡድን ጥቅም ሲባል የሕዝብን ሠላም፣ የፕሪቶሪያን ስምምነት፣ የአገሪቱን መረጋጋት እንደ መያዣ ከተጠቀመ አካል" ጋር እንዳይደራደሩ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ጠየቁ።ክፍፍል ውስጥ በገቡት የህወሓት ክንፎች ምክንያት ቀውስ ውስጥ የገባውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሚመሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን ያሉት ሐሙስ መጋቢት 4፤ 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።


በትግራይ በህወሓት አመራሮች ያለው አለመግባባት ተባብሶ ወደ ኃይል እርምጃ እያመራ ይገኛል። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ክስተት "እብደት" በማለት ድርጊቱ ክልሉን ወደ አደገኛ ሁኔታ ሊወስደው ይችላል ሲሉ እያስጠነቀቁ ነው። ባለፉት ቀናት ከተከሰቱን ሁኔታዎች ጋር አቶ ጌታቸው የት እንዳሉ፣ የፌደራል መንግሥት ድጋፍን ስለመጠየቃቸው እና ስለሌሎችም ጉዳዮች ለቢቢሲ ኒውስ ምላሽ ሰጥተዋል።




